በኢትዮጵያ ዋንጫ ቦዲቲ ከተማ ባህር ዳር ከተማን በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ አለፈ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ ዋንጫ ቦዲቲ ከተማ ባህር ዳር ከተማን በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ አለፈ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋንጫ የሶስተኛ ዙር መርሃ ግብር ቦዲቲ ከተማ ባህር ዳር ከተማን በመለያ ምት አሸንፏል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሳምሶን ቆልቻ በ21ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠራት ግብ ቦዲቲ ከተማን መሪ አድርጋለች።
አናንያ ጌታቸው በ35ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ባሳረፋት ጎል ባህር ዳር ከተማ አቻ ሆኗል።
ጨዋታው በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት በመጠናቀቁ ወደ መለያ ምት ያመራ ሲሆን ቦዲቲ ከተማ 6 ለ 5 አሸንፏል።
ውጤቱንም ተከትሎ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሚወዳደረው ቦዲቲ ከተማ ነጌሌ አርሲን ተከትሎ ለሩብ ፍጻሜ ያለፈ ሁለተኛ ቡድን ሆኗል።
በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ መድን ከቢሾፍቱ ከተማ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም፣ መቻል ከድሬዳዋ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል።