በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል አዲስ አበባ ከተማን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል አዲስ አበባ ከተማን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መቻል አዲስ አበባ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተደረገው መዲና አወል እና ቤዛዊት ንጉሴ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በሊጉ ስምንተኛ ድሉን ያስመዘገበው መቻል በ26 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ዘጠነኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አበባ ከተማ በአምስት ነጥብ የመጨረሻውን 14ኛ ደረጃን ይዟል።
ዛሬ በተደረገ የ12ኛ ሳምንት ጨዋታ ቦሌ ክፍለ ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።