ቀጥታ፡

ነጌሌ አርሲ በኢትዮጵያ ዋንጫ ለሩብ ፍጻሜ ያለፈ የመጀመሪያው ክለብ ሆኗል 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦  የኢትዮጵያ ዋንጫ ሶስተኛ ዙር ዛሬ ተጀምሯል።

ረፋድ ላይ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው የመጀመሪያ ጨዋታ ነጌሌ አርሲ አቃቂ ክፍለ ከተማን 4 ለ 0 አሸንፏል።

ርሆቦት ሰላሎ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር አለኝታ ማርቆስ እና ሀቢብ ከማል ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። 


 

ውጤቱን ተከትሎ ነጌሌ አርሲ በኢትዮጵያ ዋንጫ ለሩብ ፍጻሜ ያለፈ የመጀመሪያው ክለብ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ዋንጫ የመጀመሪያ ቀን ቀሪ ጨዋታዎች ከቀትር በኋላ ይካሄዳሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም