በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ቦሌ ክፍለ ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ቦሌ ክፍለ ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ቦሌ ክፍለ ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይቷል።
ጨዋታው ረፋድ ላይ በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ተካሄዷል።
ሃዋሳ ከተማ በ26 ነጥብ ደረጃውን ከሶስተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል። ቦሌ ክፍለ ከተማ በ20 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።
ከቀኑ 7 ሰዓት አዲስ አበባ ከተማ ከመቻል በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ይጫወታሉ።