የኢትዮጵያ ዋንጫ ሶስተኛ ዙር ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዋንጫ ሶስተኛ ዙር ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋንጫ ሶስተኛ ዙር መርሃ ግብር የመጀመሪያ ቀን ውሎ አራት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከነጌሌ አርሲ ከረፋዱ አራት ሰዓት፣ ባህር ዳር ከተማ ከቦዲቲ ከተማ ከቀኑ 7 ሰዓት እና ኢትዮጵያ መድን ከቢሾፍቱ ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።
በአዲስ አበባ ስታዲየም መቻል ከድሬዳዋ ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የሶስተኛ ዙር መርሃ ግብር እስከ ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።
የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ወላይታ ድቻ በአንደኛው ዙር ዙር መሰናበቱ የሚታወስ ነው።
የኢትዮጵያ ዋንጫን የሚያሸንፈው ቡድን በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።
የኢትዮጵያ ዋንጫ በ1937 ዓ.ም የተጀመረ አንጋፋ የጥሎ ማለፍ ውድድር ነው።