የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የጥበብ ስፍራዎችን እየጎበኙ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የጥበብ ስፍራዎችን እየጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የተለያዩ የጥበብ ስፍራዎችን እየጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ እንዲሁም አንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ የክልሎች የባህልና ስፖርት ቢሮ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
የኪነ ጥበብ ባለሙያዎቹ የአራዳ ፓርክ፣ የአዲስ ሲኒማ ማዕከል እንዲሁም የሙያ ኢትዮጵያ የእደ ጥበብ ስራዎች ማምረቻ ማህበር እና እንጦጦ የሚገኘውን የሰርከስ ሴንተር ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በጉብኝቱ በከተማዋ እና በሚመለከታቸው የሥራ ሀላፊዎች በመከናወን ላይ ስላሉት የልማት ስራዎችና የኪነ ጥበብ ስፍራዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል።