ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሸገር ከተማ ደረጃውን ወደ አራተኛ ከፍ ያደረገበትን ድል አስመዘገበ 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሸገር ከተማ ይርጋ ጨፌ ቡናን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው አይናለም አለማየሁ እና ሰናይት ኡራጎ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በውድድር ዓመቱ ስምንተኛ ድሉን ያስመዘገበው ሸገር ከተማ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ24 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል። 

በሊጉ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ይርጋ ጨፌ ቡና በ10 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል። 

ዛሬ በተደረጉ የ12ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ሲዳማ ቡና አርባ ምንጭ ከተማን፣ ባህር ዳር ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም