ቀጥታ፡

ዓለም አቀፍ ሁኔታን ያገናዘበ የጤና ስርዓት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ሰው ሰራሽ አስተውሎት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ ዓለም አቀፍ ሁኔታን ያገናዘበ የጤና ስርዓት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ሰው ሰራሽ አስተውሎት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሒ ገለፁ።

ጤና ሚኒስቴር "የሰው ሰራሽ አስተውሎትና የቴሌ ጤና ቴክኖሎጂ ለጤናው ዘርፍ የሚኖራቸው የወደፊት ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ የባለድርሻ አካላት ውይይት አካሒዷል።


 

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሒ እንደገለፁት መንግስት የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

የጤና አገልግሎትን ከሰው ሰራሽ አስተውሎትና ቴሌ-ጤና ቴክኖሎጂ ጋር በማቀናጀት ተደራሽ እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ለህክምና አገልግሎት የሚሰበሰቡ መረጃዎች ላይ በመመስረት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማጠናከር የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን መጠቀም ጉልህ ፋይዳ አለው ብለዋል።

በተለይም በወረርሽኝና በተፈጥሮ አደጋዎች ቅድመ ትንበያና የተቀናጀ ምላሽ አሰጣጥ ላይ አይነተኛ ሚና እንዳለውም ጠቁመዋል።

የጤና ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር አዳዲስና ፈጠራ የታከለባቸው ቴክኖሎጂዎች በተገቢው መልኩ ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑንም አንስተዋል።

በ2016 ዓ.ም የተሻሻለው አዲሱ የጤና ፖሊሲ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በተገቢው መልኩ ጥቅም ላይ መዋሉን የሚደግፍ መሆኑ ለአተገባበሩ አስቻይ ሁኔታ መፍጠሩን ነው የጠቀሱት።

በተለይም ለጤና ምርመራ፣ በታካሚዎች መረጃና የህክምና ታሪክ ላይ የተመሠረተ አገልግሎት ለመስጠትና በርቀት ለሚሰሩ የቴሌ ጤና አገልግሎት መጠናከር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል።

ዓለም አቀፍ ሁኔታን ያገናዘበ የጤና ስርዓት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።


 

በጤና ሚኒስቴር የጤና ስርዓት ኢኖቬሽንና ጥራት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አባስ ሃሰን በበኩላቸው፤ የጤና አገልግሎት ጥራትን በማረጋገጥ ሒደት ባለድርሻ አካላት ያላቸው ሚና የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።

የጤናውን ዘርፍ ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ጋር አጣጥሞ ተግባራዊ ለማድረግ ለተጀመረው ጥረት በዘርፉ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።

በኢትዮ-ቴሌኮም የኢንተርፕራይዝ ሶሉዩሽን ቺፍ ኦ ማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

 

በዚህም የጤና ስርዓቱን የሚያዘምኑ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች በጤና ተቋማት ተግባራዊ መደረግ መጀመራቸውን ነው የጠቀሱት።

የጤና ተቋማትን በአንድ ቋት በማስተሳሰር መረጃን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችለው ቴክኖሎጂ በጋራ ትብብር መልማቱን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም