ባህር ዳር ከተማ በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ድሉን በማስመዝገብ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል - ኢዜአ አማርኛ
ባህር ዳር ከተማ በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ድሉን በማስመዝገብ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ባህር ዳር ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አስቴር ይርጋ በ15ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
በሊጉ ሁለተኛ ድሉን ያስመዘገበው ባህር ዳር ከተማ በሰባት ነጥብ ደረጃውን ከ14ኛ ወደ 12ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ዘጠነኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ልደታ ክፍለ ከተማ በአምስት ነጥብ ደረጃውን ከ12ኛ ወደ 13ኛ ዝቅ በማለት ወራጅ ቀጠና ውስጥ ገብቷል።
በአሁኑ ሰዓት ይርጋ ጨፌ ቡና ከሸገር ከተማ በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል።