በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና አርባ ምንጭ ከተማን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና አርባ ምንጭ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሲዳማ ቡና አርባምንጭ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የአርባ ምንጭ ከተማዋ አረጋሽ ፀጋ በ14ኛው ደቂቃ በራሷ ላይ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች።
በሊጉ አራተኛ ድሉን ያስመዘገበው ሲዳማ ቡና በ15 ነጥብ ደረጃውን ከስምንተኛ ወደ ሰባተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በስምንት ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።