የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በመቀሌ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በመቀሌ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 2/2018 (ኢዜአ)፦ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር እሁድ ታህሳስ 5 ቀን 2018 በመቀሌ ከተማ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ የውድድሩን ዝግጅት አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ፤ በጎዳና ላይ ሩጫው በአጠቃላይ 79 አትሌቶች ለመወዳደር መመዝገባቸውን ገልጿል።
ውድድሩ ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች፣ ክለቦች ፣ተቋማት፣ የግል ተወዳዳሪ አትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠር ፣ ተተኪ አትሌቶችን ማፍራት እና አትሌቶችን በሽልማት ማበረታትን አላማ ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል።
40 ዳኞች ውድድሩን እንዲመሩ መመደባቸውንና ለአሸናፊ አትሌቶች ሽልማት መዘጋጀቱ በመግለጫው ላይ ተነስቷል።
የአትሌቶች ምዝገባ እስከ ነገ ድረስ እንደሚቀጥል እና ያልተመዘገቡ ተወዳዳሪዎች እንዲመዘገቡም ፌዴሬሽኑ ጥሪ አቅርቧል።