ቀጥታ፡

የባህል ስፖርት ውድድሮች የህብረተሰቡን እሴቶች ለማስተዋወቅ ተጨማሪ አቅም ይፈጥራሉ

ጅማ፤ ታህሳስ 2/2018(ኢዜአ)፦ የባህል ስፖርታዊ ውድድሮች የህብረተሰቡን እሴቶች በማስተዋወቅ ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥሩ የጅማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስር ገለጹ።

የጅማ ዞን የወረዳዎች የባህል ስፖርት ውድድርና እና ኤግዚቢሽን መርሀ ግብር ዛሬ መካሄድ ጀመረ።


 

በመክፈቻ መርሀግብሩ ላይ የተገኙት የጅማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስር እንዳሉት፤ በዞን ደረጃ የሚካሄደው የባህል ስፖርት ውድድርና የባህል ኤግዚቢሽን  ማህበረሰባዊ እሴቶችን ሳይበረዙ ለትውልዱ ለማስተላለፍ  መደላድል ፈጥሯል።

ስፖርታዊ ውድድሩ የህብረተሰቡን ባህላዊ እሴቶች በማስተዋወቅ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸውን ለማጉላት እንደሚያግዝም ጠቁመዋል።


 

በዞኑ  ያሉትን የባህል እሴቶች ለማህበረሰባዊ ትስስር ለማዋል መሰል ኤግዚቢሽኖች ጠቀሜታቸው የጎላ መሆኑን አክለዋል።

የጅማ ዞን ስፖርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ነጉማ መኮንን በበኩላቸው፤ የባህል ስፖርት ውድድር የስፖርቱን ዘርፍ  ወንድማማችነትና እህትማማችነት የሚያጠናክር  መሆኑን ጠቁመዋል።


 

ለ13 ቀናት  በሚካሄደው የባህል ስፖርት ውድድሩ ከ20 ወረዳዎችና ከአንድ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የባህል ስፖርት ተወዳዳሪዎችና የባህል ቡድኖች  እንደሚሳተፉ  ተናግረዋል።

በአስር  የባህል  የስፖርት አይነቶች ውድድር የሚደረግ መሆኑን ገልጸው የፈረስ ግልቢያ፣ የገበጣ፣ቀስት፣ ትግል እና የገና ጨዋታ ስፖርቶች ይገኙባቸዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም