በሊጉ ተስተካካይ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ መድን ሸገር ከተማን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በሊጉ ተስተካካይ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ መድን ሸገር ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ሸገር ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አማኑኤል ኤርቦ በ48ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ድሉን ያስመዘገበው የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን በ12 ነጥብ ደረጃውን ከ14ኛ ወደ 12ኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በሊጉ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ በተመሳሳይ 12 ነጥብ በግብ ክፍያ በልጦ በ12 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል።
መርሃ ግብሩ ኢትዮጵያ መድን በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ከግብጹ ፒራሚድስ ጋር በነበረው የማጣሪያ ጨዋታ ምክንያት የተራዘመ መሆኑን የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።