ቀጥታ፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በዓለም ቅርስነት በመመዝገቡ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤ታህሳስ 1/2018 (ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በዓለም ቅርስነት በመመዝገቡ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ የወላይታ ህዝብ ጥንታዊ ስልጣኔ መገለጫ፣ የበለፀገ ታሪክ እና ከህዝቡ ማንነት ጋር ስር የሰደደ ትስስር ያለው የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል የሆነው "ጊፋታ" በዩኔስኮ (UNESCO) በይፋ በመመዝገቡ የተሰማኝን ልባዊ ደስታ ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል።


 

ጊፋታ ከአሮጌው ወደ አዲሱ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሸጋገርን የሚያበስር፤ እንዲሁም እርቅ እና ፍቅር የሚሰበክበት ታላቅ እሴት መሆኑን ገልጸዋል።

"ጊፋታ" በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ለኢትዮጵያ የቱሪዝም ዕድገት ተጨማሪ አቅም ከመፍጠሩም በላይ ድሉ ለመላው የወላይታ ህዝብ እና ለኢትዮጵያውያን በሙሉ ትልቅ ኩራት እንደሆነም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም