ቀጥታ፡

ባየር ሙኒክ ስፖርቲንግ ሊዝበንን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 30/2018(ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሊግ ሻምፒዮንስ ሊግ የስድስተኛ ጨዋታ መርሃ ግብር ዛሬ ማምሻውን ተጀምሯል።

በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ባየር ሙኒክ ስፖርቲንግ ሊዝበንን 3 ለ 1 አሸንፏል።

ሰርጌ ናብሪ፣ ሌናርት ካርል እና ጆናታን ታህ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

የባየር ሙኒኩ ተከላካይ ጆሹዋ ኪሚች በራሱ ላይ ለስፖርቲንግ ግቧን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

በውድድሩ አምስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ባየር ሙኒክ በ15 ነጥብ ደረጃውን ከሶስተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ስፖርቲንግ ሊዝበን በ10 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።

በሌላኛው መርሃ ግብር ኦሎምፒያኮስ ካይራት አልማቲን በጌልሰን ማርቲንስ ጎል 1 ለ 0 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም