ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ የክልል ፓርቲነት የምስክር ወረቀት ተሰጠው - ኢዜአ አማርኛ
ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ የክልል ፓርቲነት የምስክር ወረቀት ተሰጠው
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 30፣ 2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ የክልል ፓርቲነት የምስክር ወረቀት ሰጠ።
ቦርዱ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ለስምረት ፓርቲ ሕጋዊ የክልል ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት ኅዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም መሆኑን አስታውቋል።
የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ስምረት (ስምረት) ፓርቲ የምስረታ ጉባኤውን ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ-ም በአዲስ አበባ ማካሄዱ ይታወሳል።
የፓርቲው ፕሬዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ በጉባዔው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር፥ ፓርቲው የትግራይ ሕዝብ በህወሓት እየደረሰበት ያለውን ጫና በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የተመሰረተ መሆኑን ተናግረዋል።