በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድሬዳዋ ከተማን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድሬዳዋ ከተማን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 30/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ረፋድ ላይ በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ረድኤት አስረሳኸኝ በ43ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ ቅድስት ዘለቀ የጨዋታ ኮከብ በመባል ተመርጣለች።
በሊጉ ስምንተኛ ድሉን ያስመዘገበው የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች እየቀሩት በ25 ነጥብ ደረጃውን ከአራተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በ12 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ ረድኤት አስረሳኸኝ በሊጉ ያስቆጠረቻቸውን ግቦች ወደ ዘጠኝ ከፍ በማድረግ ከኢትዮ ኤሌክትሪኳ ዳግማዊት ሰለሞን ቀጥላ በከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
‘
የሊጉ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከቦሌ ክፍለ ከተማ ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋል።