በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ልደታ ክፍለ ከተማን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ልደታ ክፍለ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 29/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሲዳማ ቡና ልደታ ክፍለ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ምርጥነሽ ዮሐንስ፣ ኤልሳቤት ብርሃኑና ምትኬ ብርሃኑ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ፍቅርተ ካሳ ለልደታ ክፍለ ከተማ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
በሊጉ ሶስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ሲዳማ ቡና አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ12 ነጥብ ደረጃውን ከ10ኛ ወደ 8ኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ልደታ ክፍለ ከተማ በአምስት ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል።
ዛሬ በተደረጉ የ11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች መቻል ባህር ዳር ከተማን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ አዳማ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።