ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል ባህር ዳር ከተማን አሸነፈ 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 29/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሃ ግብር መቻል ባህር ዳር ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል። 

በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ እፀገነት ብዙነህ በ56ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች። 

በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ድሉን ያስመዘገበው መቻል በ23 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል። 

በአንጻሩ በሊጉ ዘጠነኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ባህር ዳር ከተማ በአራት ነጥብ የመጨረሻውን 14ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም