በፕሪሚየር ሊጉ ዎልቭስ ከማንችስተር ዩናይትድ ይጫወታሉ - ኢዜአ አማርኛ
በፕሪሚየር ሊጉ ዎልቭስ ከማንችስተር ዩናይትድ ይጫወታሉ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 29/2018 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር በዎልቭስ እና ማንችስተር ዩናይትድ መካከል ዛሬ ይካሄዳል።
የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ምሽት 5 ሰዓት ላይ በሞለኒው ስታዲየም ይደረጋል።
ዎልቭስ በሁለት ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል። ማንችስተር ዩናይትድ በ22 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ሁለቱ ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ21ኛ ጊዜ ነው።
ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 20 ጨዋታዎች ማንችስተር ዩናይትድ 10 ጊዜ ሲያሸንፍ ዎልቭስ 7 ጊዜ ድል ቀንቶታል። 3 ጊዜ አቻ ወጥቷል።
በ20ዎቹ ጨዋታዎች ማንችስተር ዩናይትድ 24 ግቦችን ሲያስቆጥር ዎልቭስ 22 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች በነበራቸው ግንኙነት ማንችስተር ዩናይትድ ሶስት ጊዜ፣ ዎልቭስ ደግሞ ሁለት ጊዜ ጨዋታዎችን አሸንፏል።
መጥፎ የውድድር ዓመት እያሳለፈ የሚገኘው ዎልቭስ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል።
ተጋጣሚው ማንችስተር ዩናይትድ በጥሩ አቋሙ ለመቀጠል ሶስት ነጥብ ያስፈልገዋል።
የ40 ዓመቱ ማይክል ሳልስበሪ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።