በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 29/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ጨዋታ አዳማ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታው በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ተካሄዷል።
አዳማ ከተማ በ14 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።
ተጋጣሚው አዲስ አበባ ከተማ በአምስት ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።