ቀጥታ፡

20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በውጭ በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ተከበረ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 29/2018(ኢዜአ)፦ 20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በውጭ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ተከብሯል።

በዓሉ የተከበረው "ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሀሳብ ነው።

በአከባበሩ ላይ የሚሲዮን መሪዎች፣ ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የማህበረሰብ ተወካዮችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ኢትዮጵያ የብዝኃነት ተምሳሌት እና ህብረ ብሄራዊ አንድነት ባሳየ መልኩ ተከብሯል።

የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦችና አልባሳት ለእይታ የቀረቡ ሲሆን የብሔሮች ብሔረሰቦች ሙዚቃዎችና ባሕላዊ ውዝዋዜዎች የሚገልጹ ሁነቶችም ቀርበዋል።

በዓሉ በቻይና፣ አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ቱርኪዬ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኳታር፣ ደቡብ ሱዳን፣ ቤልጂየም፣ ፓኪስታን፣ ኮትዲቭዋር፣ ስዊድን፣ ኮሪያ ሪፐብሊክ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ አውስትራሊያ፣ ዩጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ ቀኑ ከተከበረባቸው ሀገራት መካከል ይገኙበታል።

20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን "ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሀሳብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ዛሬ ተከብሯል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም