ቀጥታ፡

የለማች፣ የተከበረችና የታፈረች ኢትዮጵያን እናፅና - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 29/2018(ኢዜአ)፦ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በፍትህ እና በእኩልነት መሠረቶች ላይ በማዋቀር የለማች፣ የተከበረችና የታፈረች ኢትዮጵያን ማጽናት ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።

20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን "ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሀሳብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ዛሬ እየተከበረ ነው።


 

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በኤክስ ገጻቸው "ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሀሳብ ለ20ኛ ጊዜ ለሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።


 

ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን በፍትህና በእኩልነት መሠረቶች ላይ በማዋቀር የለማች፣ የተከበረችና የታፈረች ኢትዮጵያን እናፅና ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም