ቀጥታ፡

በደሴ ታላቅ የሰላም ጥሪን ያነገበ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

ደሴ ፤ ሕዳር 29/2018(ኢዜአ )፡- በደሴ ከተማ አስተዳደር  ታላቅ የሰላም ጥሪን ያነገበ ሰላማዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ነዋሪዎችና ሌሎችም እየተሳተፉበት የሚገኘው የድጋፍ ሰልፉ በደቡብ ወሎ  ዞን የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል።

የሰልፉ ተሳታፊዎች፤ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የድርሻችንን እንወጣለን፣ ልማታችንን በጋራ እናስቀጥላለን፣ አንድነታችንንም እናጠናክራለን ፣ቤተ እምነቶች ሰላምን ማስፈን ተቀዳሚ ተግባራቸው ነው፣ የሰላምና የመከባበር ባሕልን ለማስቀጠል የሃይማኖት ተቋማት ሚና ከፍተኛ ነው  የሚሉና ሌሎችንም መልዕክቶች እያስተላለፉ ነው።


 

ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡት ሰልፈኞቹ  በአሁኑ ወቅት ወደ ሆጤ ስታዲየም በማምራት ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም