20 ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
20 ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፤ ህዳር 29/2018(ኢዜአ):- 20ኛው የኢትዮጵያ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ እየተከበረ ነው።
'ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት' በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ በሚገኘው በዓል ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ታድመዋል።
በዓሉ መላው ኢትዮጵያውያንን የሚያስተሳስር፣ ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ የጋራ ተግባቦት በመፍጠር ለኢትዮጵያ ማንሰራራት ጉዞ ምቹ መደላድል የሚፈጠርበት መሆኑ ተገልጿል።