ቀጥታ፡

የቤት አቅርቦትን ለመጨመር በግሉ ዘርፍ የሚደረጉ ጥረቶችን ማበረታታት አስፈላጊ ነው

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 28/2018 (ኢዜአ)፦የቤት አቅርቦትን ለመጨመር በግሉ ዘርፍ የሚደረጉ ጥረቶችን ማበረታታት አስፈላጊ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ከንቲባዋ ዛሬ ፊሶን ሪል እስቴት እየገነባቸው ያሉትን 1,000 ቤቶች ተዘዋውረን ተመልክተናል ብለዋል።

እየተገነቡ ያሉት ቤቶች የከተማችንን ደረጃ ለማሻሻል የምንተገብረውን የግንባታ ስታንዳርድ የሚያሟሉ፣ ጥራታቸዉን የጠበቁ  መሆናቸውን በጉብኝታችን አይተናል ነው ያሉት።

ይህ ደግሞ ለኮፕ 32 ተሳታፊዎች አገልግሎት ለመስጠት ተጨማሪ  አቅም የሚፈጥር ነው እንደሆነም ጠቁመዋል::

በዘርፉ የተሰማራችሁ የከተማችን አልሚዎች፣ እየገነባችሁ ያላችሁና ለኮፕ 32 እያደረጋችሁ ያለውን አጠቃላይ ቅድመ ዝግጅት በየክፍለ ከተማችሁ ብታሳውቁ የበለጠ ተቀራርቦ ለመስራት እና ጉባኤዉንም የበለጠ ዉጤታማ ለማድረግ  ያግዛል።

ለጉባኤው ወደ አገራችን የሚመጡ እንግዶቻችንን በትብብር ለማስተናገድ እና ለጉባኤዉ ዉጤታማነት በጋራ እንስራ ፣ ከወዲሁ እንዘጋጅ በማለት ለአልሚዎች ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም