ቀጥታ፡

ለብሄር ፤ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል አከባበር የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማት እውቅና ተሰጠ

ሆሳዕና፤ ሕዳር 28/2018(ኢዜአ)፡-  የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለ20ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል አከባበር የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማት እውቅና  ሰጠ።

እውቅና ከተሰጣቸው መካከል የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ፌዴራል ፖሊስ፣ የትምህርት ሚኒስቴርን ጨምሮ ሌሎችም ይገኙበታል። 

ከሚዲያ ተቋማትም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ጨምሮ ሌሎችም ብሄራዊና ክልላዊ የሚድያ ተቋማት እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ 

ተቋማቱ እውቅናውን ከፌዴሬሽን  ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ተቀብለዋል።

#Ethiopian_News_Agency  #ኢዜአ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም