አርባምንጭ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ተጋርተዋል - ኢዜአ አማርኛ
አርባምንጭ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ተጋርተዋል
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 28/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታ አርባምንጭ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታው ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተከናውኗል።
ውጤቱን ተከትሎ አርባምንጭ ከተማ በአምስት ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ይዟል።
አርባምንጭ በሊጉ ምንም ጨዋታ አላሸነፈም።
ኢትዮጵያ ቡና በ11 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ጨዋታውን ተከትሎ የዘጠነኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።
ፕሪሚየር ሊጉ በኢትዮጵያ ዋንጫ አራተኛ ዙር ጨዋታዎች ምክንያት የሚቋረጥ ሲሆን ውድድሩ ታህሳስ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በ10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ይመለሳል።