ቀጥታ፡

ፋሲል ከነማ  እና መቀሌ 70 እንደርታ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 28/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታ ፋሲል ከነማ እና መቀሌ 70 እንደርታ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ናትናኤል ማስረሻ በ89ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ፋሲል ከነማ መሪ ሆኗል።

ፍጹም ዓለሙ በ92ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ግብ መቀሌ 70 እንደርታ በባከነ ሰዓት ወሳኝ አንድ ነጥብ እንዲያገኝ አስችሎታል።

ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ፋሲል ከነማ ነጥቡን ወደ 17 ከፍ አድርጓል። ቡድኑ ከሊጉ መሪ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት የማጥበብ እድል አልተጠቀመበትም።


 

መቀሌ 70 እንደርታ በአምስት ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

መቀሌ በሊጉ እስከ አሁን ምንም ጨዋታ አላሸነፈም።

በአሁኑ ሰዓት አርባምንጭ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም