ነጌሌ አርሲ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
ነጌሌ አርሲ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 28/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታ ነጌሌ አርሲ ሀዲያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ከቤ ብዙነህ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥሯል።
እዮብ አለማየሁ ለሀዲያ ሆሳዕና ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በሊጉ ሶስተኛ ድሉን ያስመዘገበው አዲስ አዳጊው ነጌሌ አርሲ በ13 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።
በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሀዲያ ሆሳዕና በሰባት ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።