ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ከዚህ ቀደም የት የት ተከበረ?

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን መከበር ከጀመረ ዘንድሮ 20ኛ ዓመቱን ይዟል። ለመሆኑ እስካሁን የት የት ተከበረ?

✍️ በ1999 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በፌደሬሽን ምክር ቤት አስተናጋጅነት

✍️በ2000 ዓ.ም በቀድሞው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አስተናጋጅነት

✍️ በ2001 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት

✍️ በ2002 ዓ.ም በድሬዳዋ አሥተዳደር አስተናጋጅነት

✍️ በ2003 ዓ.ም በፌደሬሽን ምክር ቤት አስተናጋጅነት

✍️ በ2004 ዓ.ም በትግራይ ክልል አስተናጋጅነት

✍️ በ2005 ዓ.ም በአማራ ክልል አስተናጋጅነት

✍️ በ2006 ዓ.ም በሶማሌ ክልል አስተናጋጅነት

✍️ በ2007 ዓ.ም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አስተናጋጅነት

✍️ በ2008 ዓ.ም በጋምቤላ ክልል አስተናጋጅነት

✍️ በ2009 ዓ.ም በሐረሪ ክልል አስተናጋጅነት

✍️ በ2010 ዓ.ም በአፋር ክልል አስተናጋጅነት

✍️በ2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አስተናጋጅነት

✍️ በ2012 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት

✍️ በ2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተናጋጅነት

✍️ በ2014 ዓ.ም በድሬዳዋ አሥተዳደር አስተናጋጅነት

✍️ በ2015 ዓ.ም በሲዳማ ክልል አስተናጋጅነት

✍️ በ2016 ዓ.ም በሶማሌ ክልል አስተናጋጅነት

✍️ በ2017 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አስተናጋጅነት

✍️ በ2018 ዓ.ም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስተናጋጅነት በሆሳዕና ከተማ “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሐሳብ በነገው እለት ሕዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚከበር በፌደሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ቡድን መሪ እስራኤል ማናዬ ለኢዜአ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም