የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከት የተዘጋጀ ሲምፖዚየም መካሄድ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከት የተዘጋጀ ሲምፖዚየም መካሄድ ጀመረ
ሆሳዕና ፤ ሕዳር 28/2018 (ኢዜአ)፡-20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ሲምፖዚየም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ መካሄድ ጀመረ። ፡
20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ነገ በሀገር አቀፍ ደረጃ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አዘጋጅነት በሆሳዕና ከተማ እንደሚከበር ይታወቃል።
ሲምፖዚየሙ " ዴሞክራሲያዊ መግባባት ፣ ለሕብረ ብሄራዊ አንድነት " በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ መሆኑ ተመልክቷል።
በዚህም በፌዴራሊዝም ፅንሰ ሀሳብ ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ይጠበቃል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ፤ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች ፡ የባሕል አምባሳደሮችና ተጋባዥ እንግዶች እየተሳተፉ ነው፡፡