ቀጥታ፡

ስድስት ግቦች በተቆጠሩበት ጨዋታ ሊቨርፑል እና ሊድስ ዩናይትድ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት ጨዋታ ሊቨርፑል እና ሊድስ ዩናይትድ ሶስት አቻ ተለያይተዋል።

ማምሻውን በኢላንድ ሮድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፈረንሳዊው አጥቂ ሁጎ ኢኪቲኬ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ዶምኒክ ስቦዝላይ ቀሮዋን ጎል ለሊቨርፑል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

አንቶን ስታች እና አኦ ታናካ በጨዋታ እንዲሁም ዶምኒክ ካልቨርት-ሉዊን በፍጹም ቅጣት ለሊድስ ዩናይትድ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በጨዋታው ሊቨርፑል ሁለት ጊዜ መርቶ ውጤቱን አለማስጠበቁ ዋጋ አስከፍሎታል።

ሊቨርፑል በ23 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሊድስ ዩናይትድ በበኩሉ በ15 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል።

#Ethiopian_News_Agency  #ኢዜአ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም