በመዲናዋ የተሰሩ የልማት ስራዎች የዜጎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ተጨባጭ ውጤቶች እያስመዘገቡ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በመዲናዋ የተሰሩ የልማት ስራዎች የዜጎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ተጨባጭ ውጤቶች እያስመዘገቡ ነው
አዲስ አበባ፤ ህዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የተሰሩ የልማት ስራዎች የዜጎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ተጨባጭ ውጤቶች እያስመዘገቡ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመደመር መንግሥት ዕይታ፥ የዘርፎች እመርታ የ3ኛ ዙር ሰልጣኞች ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመደመር መንግሥት ዕይታ፥ የዘርፎች እመርታ የ3ኛ ዙር የከተማዋ ሰልጣኞች የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም በመዲናዋ በተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን የኮልፌ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አንዋር አብዱ በመዲናዋ የተሰሩ የልማት ስራዎች የቱሪዝም መስህብነትን የሚያሳድጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ የአራዳ ክፍለ ከተማ የኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ሀላፊ ቅድስት ደሳለኝ በበኩላቸው፤ በመዲናዋ የተሰሩት የልማት ስራዎች የከተማውን ገጽታ የቀየሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በመዲናዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ወንጀሎች ሚሰሩባቸው ቦታዎችን በማጥፋት ትልቅ ችግርን ያቃለለ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 12 ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ኢንስፔክተር ሁሴን ኢንካ ናቸው።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን የኮልፌ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አንዋር አብዱ፤ የመደመር መንግሥት በዘርፎች ላይ የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተጨባጭ ውጤቶች እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽህፈት ቤት ሀላፊ መስከረም ሙለታ በከተማዋ የተገነቡ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ለትውልድ የሚሻገሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።