ሸገር ከተማ ባህር ዳር ከተማን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
ሸገር ከተማ ባህር ዳር ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት ሸገር ከተማ ባህር ዳር ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አንተነህ ተፈራ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ያሬድ መኮንን ቀሪዋን ጎል ለሸገር ከተማ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ሄኖክ ይበልጣል ለባህር ዳር ከተማ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።
በሊጉ ሶስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ሸገር ከተማ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ12 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ባህር ዳር ከተማ በተመሳሳይ 12 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ቀን ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች አዳማ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ኢትዮጰያ ንግድ ባንክን 2 ለ 1 ሲያሸንፉ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከድሬዳዋ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይቷል።