ቀጥታ፡

ማንችስተር ሲቲ ሰንደርላንድን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ሰንደርላንድን 3 ለ 0 አሸንፏል። 

ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሩበን ዲያዝ፣ ጆሽኮ ግቫርዲዮል እና ፊል ፎደን ግቦቹን አስቆጥረዋል።

የሰንደርላንዱ ሉክ ኦኒየን በ95ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። 

በሊጉ 10ኛ ድሉን ያስመዘገበው ማንችስተር ሲቲ በ31 ነጥብ የሁለተኛ ደረጃን ከአስቶንቪላ ተረክቧል።

ሰማያዊዎቹ ከሊጉ አርሰናል ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ዝቅ አድርገዋል። 

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ሰንደርላንድ በ23 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል። 

በሌሎች መርሃ ግብሮች ቦርንማውዝ እና ቼልሲ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ኤቨርተን ኖቲንግሃም ፎረስትን  3 ለ 0 ሲረታ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ብሬንትፎርድን 2 ለ 0 እና ኒውካስትል ዩናይትድ በርንሌይን  2 ለ 1 አሸንፈዋል።

ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ ሊድስ ዩናይትድ ከሊቨርፑል ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም