ቀጥታ፡

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከድሬዳዋ ከተማ አቻ ተለያየ 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል። 

ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሂዷል። 

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ነጥቡን ወደ 20 ከፍ አድርጓል። ከተከታዩ ፋሲል ከነማ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት የማስፋት እድሉን አልተጠቀመበትም። 

ድሬዳዋ ከተማ በ12 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም