አዳማ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
አዳማ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 27/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታ አዳማ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሙጂብ ቃሲም በአምስተኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
በሊጉ አራተኛ ድሉን ያስመዘገበው አዳማ ከተማ በ16 ነጥብ ደረጃውን ከስምንተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ15 ነጥብ ከነበረበት አራተኛ ደረጃ ወደ አምስተኛ ዝቅ ብሏል።