ቀጥታ፡

አስቶንቪላ የሊጉ መሪ አርሰናልን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 26/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብር አስቶንቪላ አርሰናልን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በቪላ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማቲ ካሽ በ36ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ አስቶንቪላን መሪ አድርጓል።

ሊያንድሮ ትሮሳርድ በ52ኛው ደቂቃ በግሩም ሁኔታ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ግብ አርሰናል አቻ ሆኗል።

95ኛው ደቂቃ ላይ ኤሚሊያኖ ቡንዲያ ያስቆጠራት ጎል አስቶንቪላን አሸናፊ አድርጓል።

ጨዋታው ጠንካራ ፉክክር ተደርጎበታል።

በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው የሊጉ መሪ አርሰናል 33 ነጥብ ላይ ረግቷል።

በሊጉ ዘጠነኛ ድሉን ያስመዘገበው አስቶንቪላ በ30 ነጥብ ደረጃውን ከሶስተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም