በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ከተማን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ከተማን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 26/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ከተማን 4 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ረድኤት አስረሳኸኝ ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር እፀገነት ግርማ እና ምርቃት ፈለቀ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ድሉን በማስመዝገብ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች እየቀሩት በ22 ነጥብ ደረጃውን ከአራተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በሊጉ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አበባ ከተማ በአራት ነጥብ የመጨረሻውን 14ኛ ደረጃን ይዟል።
በአሁኑ ሰዓት ድሬዳዋ ከተማ እና ቦሌ ክፍለ ከተማ በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል።