በሐረሪ ክልል በሁሉም ዘርፎች የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ጎልብቷል - ኢዜአ አማርኛ
በሐረሪ ክልል በሁሉም ዘርፎች የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ጎልብቷል
ሐረር ፤ህዳር 26/2018 (ኢዜአ) ፡-በሐረሪ ክልል በሁሉም ዘርፎች የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን በብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ አብዱልሃኪም ኡመር አመለከቱ።
ለክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ ሴት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
በብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ሕህፈት ቤት ሴቶች ክንፍ ባዘጋጀው ስልጠና ላይ የተገኙት በፓርቲው የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ አብዱልሃኪም ኡመር እንዳሉት በክልሉ በሁሉም ዘርፎች የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እየጎለበተ መጥቷል።
በተለይም የክልሉ ሴቶች በሰላም ግንባታ እንዲሁም ልማትና መልካም አስተዳደርን ጨምሮ በሰው ተኮር ተግባራት ሚናቸውን በአግባቡ እየተወጡ መሆኑን ገልፀዋል።
በክልሉ ይህንኑ ተግባራት ከማጎልበት ባለፈ ሁለተናዊ የሴቶች ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ይበልጥ ለማሳደግ የሚያግዙ የአቅም ግንባታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው መድረኩም የዚሁ አካል ነው ብለዋል።
ስልጠናው የአመራር ብቃትን ከማጎልበት አንፃር ፋይዳው የጎላ መሆኑን የጠቆሙት አቶ አብዱልሃኪም በተለይም በክልሉ በአመራርነት የሚገኙ ሴቶች ሌሎችን የማብቃት ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ የሴቶች ክንፍ ሃላፊ ዚነት ዩስፍ በበኩላቸው በክልሉ ሴቶች በሁሉም ዘርፎች ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።
የሴቶችን ብቃት ለማጎልበት የተቀናጀ እንቅስቃሴ እየተደረገ ስለመሆኑም አንስተዋል።
በስልጠናው መሰረታዊ የአመራርነት ብቃትና ኮሙኒኬሽን ዙሪያ ከፍተኛ ሴት አመራሮችን ለማብቃት ያለመ መሆኑንም ተናግረዋል።
በስልጠናው የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ ሴት አመራሮች ተገኝተዋል።