ማንችስተር ዩናይትድ እና ዌስትሃም ዩናይትድ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ዩናይትድ እና ዌስትሃም ዩናይትድ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 25/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ እና ዌስትሃም ዩናይትድ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ማምሻውን በኦልድትራፎርድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዲያጎ ዳሎት በ58ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ማንችስተር ዩናይትድ መሪ ሆኗል።
ሳውንጎቱ ማጋሳ በ83ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ግብ ዌስትሃምን አቻ አድርጓል።
በጨዋታው ላይ ብልጫ ወስዶ የተጫወተው ማንችስተር ዩናይትድ ውጤቱን አስጠብቆ መውጣት አልቻለም።
ማንችስተር ዩናይትድ በ22 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።
ተጋጣሚው ዌስትሃም ዩናይትድ በ12 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።