በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ባህር ዳር ከተማን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ባህር ዳር ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 25/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አዳማ ከተማ ባህር ዳር ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ምስር ኢብራሂም ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር ነጻነት መና ቀሪዋን ጎል ለአዳማ ከተማ ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
ወርቅነሽ መሰለ ለባህር ዳር ከተማ ብቸኛውን ግብ አስቆጥራለች።
በሊጉ አራተኛ ድሉን ያስመዘገበው አዳማ ከተማ በ13 ነጥብ ደረጃውን ከስምንተኛ ወደ ስድስተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ባህር ዳር ከተማ በአራት ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
በአሁኑ ሰዓት መቻል እና ልደታ ክፍለ ከተማ በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው።