እስካሁን በ195 ሺህ 336 ሔክታር ላይ የነበረ ሰብል ተሰብስቧል - ኢዜአ አማርኛ
እስካሁን በ195 ሺህ 336 ሔክታር ላይ የነበረ ሰብል ተሰብስቧል
አዲስ አበባ፤ሕዳር 25/2018(ኢዜአ)፡- በ2017/18 የመኸር ወቅት በተለያዩ ሰብሎች ከለማው ውስጥ በ195 ሺህ 336 ሔክታር የነበረ ሰብል መሰብሰቡን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ።
ከተሰበሰበው ሰብልም 24 ሚሊየን 148 ሺህ 273 ኩንታል ምርት መገኘቱን የቢሮው ምክትልና የእርሻ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አድማሱ አወቀ ለኢዜአ ተናግረዋል።
በምርት ዘመኑ ከለማው ውስጥ 232 ሺህ 568 ሔክታር በኩታገጠም መልማቱን ጠቅሰዋል።
በክላስተር ከለማው ውስጥም በ57 ሺህ 705 ሔክታር ላይ የነበረ ሰብል ተሰብስቦ፤ 4 ሚሊየን 633 ሺህ 58 ኩንታል ምርት መገኘቱን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በግል ባለሃብቶች በተለያዩ ሰብሎች ከለማው 32 ሺህ 864 ሔክታር ውስጥ በ27 ሺህ 801 ሔክታር ላይ የነበረ ሰብል መሰብሰቡን ገልጸዋል።
ከዚህም 4 ሚሊየን 754 ሺህ 931 ኩንታል ምርት መገኘቱን ነው ያረጋገጡት።
የሰብል ስብሰባው ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቅሰው፤ አርሶ አደሩ ብክነት በማያስከትል ሁኔታ የደረሱ ሰብሎችን በጊዜና በጥንቃቄ እንዲሰበስብ አሳስበዋል።
በምርት ዘመኑ በተለያዩ ሰብሎች ከለማው 763 ሺህ 424 ሔክታር ውስጥ 69 ሚሊየን 760 ሺህ 768 ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን አውስተዋል።