ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 25/2018 (ኢዜአ):- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ክላቨር ጋቴቴ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ክላቨር ጋቴቴ ጋር እ.ኤ.አ በ2027 አፍሪካን በሚገባ የሚወክል ኮፕ32 በማዘጋጀት ረገድ በጋራ ስለምንሰራባቸው መንገዶች ተወያይተናል ብለዋል።


 

የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ብሎም ዋና ፀሐፊው ከቡድናቸው ጋር በመሆን ኮፕ32 ስኬታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ እተማመናለሁ ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም