የግብርና ሚኒስትር፣ የሰላም ሚኒስትር እና የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሹመቶች በምክር ቤት ጸደቀ - ኢዜአ አማርኛ
የግብርና ሚኒስትር፣ የሰላም ሚኒስትር እና የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሹመቶች በምክር ቤት ጸደቀ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 25/2018(ኢዜአ)፦ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ፣ የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ እና የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቢኒያም ኤሮ ሹመቶች በምክር ቤት ጸድቀዋል።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው።
ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የተሾሙት የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ እና የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ ሹመቶችን አፅድቋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የተመደቡት ቢንያም ኤሮ ሹመት በምክር ቤት ፀድቋል።
የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ፣ የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ እና የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቢኒያም ኤሮ በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።
ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011ን ለማሻሻል የቀረበ አዋጅን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።