በፕሪሚየር ሊጉ ማንችስተር ዩናይትድ ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር ይጫወታል - ኢዜአ አማርኛ
በፕሪሚየር ሊጉ ማንችስተር ዩናይትድ ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር ይጫወታል
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 25/2018 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ በማንችስተር ዩናይትድ እና ዌስትሃም ዩናይትድ መካከል ዛሬ ይደረጋል።
ጨዋታው ምሽት 5 ሰዓት ላይ በኦልትራፎርድ ስታዲየም ይካሄዳል።
ባለሜዳው ማንችስተር ዩናይትድ በ21 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ተጋጣሚው ዌስትሃም ዩናይትድ በ11 ነጥብ 18 ደረጃን በመያዝ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ሁለቱ ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ67ኛ ጊዜ ነው።
ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 66 ጨዋታዎች 38 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ሲይዝ ዌስትሃም ዩናይትድ 13 ጊዜ ድል ቀንቶታል። በቀሪ 15 ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።
በ66ቱ ጨዋታዎቹ ላይ ማንችስተር ዩናይትድ 88 ግቦችን ሲያስቆጥር ዌስትሃም ዩናይትድ በበኩሉ 53 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ባለፉት 10 የሊግ ጨዋታዎች በነበራቸው ግንኙነት ማንችስተር ዩናይትድ አራት ጊዜ ሲያሸንፍ ዌስትሃም ዩናይትድ ደግሞ ሁለት ጨዋታዎችን በድል ተወጥቷል። አራት ጊዜ ደግሞ ነጥብ ተጋርተዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ደረጃውን ማሻሻል የሚችልበት እድል ያገኛል።
በአንጻሩ ዌስትሃም ዩናይትድ ሶስት ነጥብ ከወራጅ ቀጠና እንዲወጣ ያስችለዋል።
የ29 ዓመቱ አንድሪው ኪችን ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።