ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 25/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ይደረጋሉ።  

ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ ባህር ዳር ከተማ ከአዳማ ከተማ ይጫወታሉ። 

ባህር ዳር ከተማ በሊጉ ካከናወናቸው ዘጠኝ ጨዋታዎች መካከል ያሸነፈው አንዱን ብቻ ነው። ሰባት ጊዜ ሲሸነፍ በቀሪው አንድ ጨዋታ ነጥብ ተጋርቷል። አራት ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ 12 ጎሎች ተቆጥረውበታል።

ቡድኑ በአራት ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። 

ተጋጣሚው አዳማ ከተማ እስከ አሁን በሊጉ ባካሄዳቸው ስምንት ጨዋታዎች ሶስቱን ሲያሸንፍ በአምስቱ ተሸንፏል። በቀሪ አንድ ጨዋታ አቻ ተለያይቷል። ስድስት ግቦችን በነዚህ ጨዋታዎች ከመረብ ላይ ሲያገናኝ 18 ጎሎች ተቆጥረውበታል።

አዳማ ከተማ በ10 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።በሌላኛው መርሃ ግብር መቻል ከልደታ ክፍለ ከተማ ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። 

በውድድር ዓመቱ ካደረጋቸው ዘጠኝ ጨዋታዎች መካከል አምስቱን ያሸነፈው መቻል በሁለት ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዷል። ሁለት ጊዜ ደግሞ ነጥብ ተጋርቷል። 14 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ ሰባት ጎሎችን አስተናግዷል።

መቻል በ17 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

ተጋጣሚው ልደታ ክፍለ ከተማ በሊጉ ባካሄዳቸው  ዘጠኝ ጨዋታዎች መካከል ማሸነፍ አንድ ጊዜ ሲያሸንፍ ስድስት ጊዜ ተሸንፏል።  ሁለት ጊዜ ደግሞ ነጥብ ተጋርቷል። በጨዋታዎቹ ሰባት ግቦችን ሲያስቆጥር 16 ግቦችን አስተናግዷል።

ቡድኑ በአምስት ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም