ቀጥታ፡

ሰላም በዘላቂነት እንዲሰፍን ተሳትፏችንን  አጠናክረን እንቀጥላለን- የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች 

ጎንደር፤ ሕዳር 25/2018(ኢዜአ)፡- ሰላም  በዘላቂነት  እንዲሰፍን   በመደገፍ  ተሳትፏቸውን  አጠናክረው  እንደሚቀጥሉ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። 

የጎንደር ከተማ አስተዳደርና የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ  ያዘጋጁት ታላቅ የሰላም ጥሪን ያነገበ ሕዝባዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ  እየተካሄደ ነው።


 

የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ  ሌሎችም ነዋሪዎች በድጋፍ ሰልፉ በመሳተፍ ላይ  ናቸው። 


 

የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊ ነዋሪዎች፤ ሰላም  በዘላቂነት  እንዲሰፍን   በመደገፍ  ተሳትፏቸውን እንደሚያጠናክሩና  ሰላምን መስበካቸውን እንደሚቀጥሉ የሚገልጹ የተለያዩ መልዕክቶችን እያስተላለፉ ነው።

ከመልዕክቶቹም  ቤተ እምነቶች ሰላምን ማስፈን ተቀዳሚ ተግባራቸው ነው፣  የሰላምና የመከባበር ባሕልን ለማስቀጥል የሃይማኖት ተቋማት ሚና የማይተካ ነው፣  ሀይማኖታዊ እሴቶቻችን የአብሮነትና የጥንካሬያችን  መሰረቶች ናቸው የሚሉ ይገኙበታል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም