አርሰናል ብሬንትፎርድን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ - ኢዜአ አማርኛ
አርሰናል ብሬንትፎርድን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 24/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርሰናል ብሬንትፎርድን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማይክል ሜሪኖ በ11ኛው እና ቡካዮ ሳካ በ91ኛው ደቂቃ ላይ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
በጨዋታው አርሰናል ከተጋጣሚው ጠንካራ ፈተና ቢገጥመውም ወሳኝ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
በውድድር ዓመቱ 10ኛ ድሉን ያስመዘገበው አርሰናል በ33 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል።
ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በሊጉ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ብሬንትፎርድ በ19 ነጥብ ከነበረበት 10ኛ ደረጃ ወደ 13ኛ ዝቅ ብሏል።